ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱአስታውቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም ከዜጎች ደህንነት ጋር በተያያዘ ብዙ ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሶስት ወራት በፊት ለዚህ ምክር ቤት ሪፖርት እያቀረቡ እያሉ ስልጣን እንዲለቁ ተጠይቀው ነበር።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *