ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቡና ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ጨዋታ የሊጉ መሪ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና አገናኝቷል።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

እስማኤል ኦሮ አጎሮ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ብሩክ በየነ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ከመቻል ጋር እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ተብሏል።

ከአራት ቀናት በኋላም ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና፣ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ መድህን እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ59 ነጥቦች ሲመራ ባህርዳር በ54 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በ48 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የወራጅነት ደረጃዎች ላይ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ13 ነጥብ እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ በተመሳሳይ በ13 ነጥብ የመጨረሻዎቹን ሁለት ደረጃዎች ሲይዙ ወልቂጤ ከተማ በ33 ነጥብ ሌላኛው ወራጅነት ቀጠና ያለው ክለብ ሆኗል።

የኮኮብ ግብ አግቢነት ደረጃውን የቅዱስ ጊዮርጊሱ እስማኤል አጎሮ በ24 ጎሎች፣ የወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ በ18 እንዲሁም የድሬዳዋው ቢንያም ጌታቸው ደግሞ በ12 ጎሎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን የኮኮብ ግብ አግቢነት ደረጃን ይዘዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *