ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡

ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡

ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡

ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ ተመርቋል፡፡

መጽሃፎቹን በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መርቀዋል፡፡

ቻይና አምርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ እንዲሰጥ ከዚህ በፊት የወሰነች ሲሆን የቻይና ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የአማርኛ ቋንቋ ከሩሲያ እና ቻይና በተጨማሪ በአሜሪካ፣ ጀርመን እና ሌሎችም ሀገራት በመሰጠት ላይ ሲሆን ኢትዮጵያም የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን ለዜጎቿ በስርዓት ትምህርቷ ላይ አካታ በማስተማር ላይ ትገኛለች፡፡

አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የስራ ቋንቋ ሲሆን ኦሮሚኛ፣ ትግሪኛ እና ሶማሊኛ ተጨማሪ ያስራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡  

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *