በጉና ተራራ ላይ የህዋ ማዕከል የመገንባት እቅድ እንዳለ ተገለጸ



የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በአፄ ቴውድሮስ የተሰየመች ሮኬት ለኹለተኛ ጊዜ ማስወንጨፉ ይታወሳል።

ዩንቨርሲቲው በከተማዋ አቅራቢ በሚገኘው የጉና ተራራ ላይ የህዋ ምርምር ማዕከል ለመገንባት እቅድ መያዙን ገልጿል።

154ኛውን የአፄ ቴዎድሮስ ዝክረ-ሰማዕት መታሰቢያ በዓል አስመልክቶ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ በአካባቢያቸው ባለ ቁሳቁስ ከ 2 ኪ.ሜትር በላይ መወንጨፍ የቻለች ሮኬት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ዓመት በፊት አስወንጭፏል።

ዩንቨርሲቲው በዚህ ዓመትም በተሻለ መልኩ ማስወንጨፍ መቻላቸውን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አዲሱ ወርቁ እንዳሉት በ2014 የተሰሩት ሮኬትና መድፍ  ዋና አላማ የአጼ ቴዎድሮስን የመቅደላ መድፍን ለመድገምና ኢትዮጽያ ውስጥ የተሳካለት ሮኬትና መድፍ መስራት መቻል እንደሆነ ተናግረዋል። 

ሚያዚያ 2014 በሮኬት ሳይንስ ማዕከል አሞራ ገደል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተወነጨፈችው ሮኬት የት ማረፍ እንዳለባት የሚቆጣጠር ማሽን ስለሌለን ከፈለገችው ቦታ ነበር ያረፈችው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በ2015 ግንቦት ወር ላይ የተወነጨፈችው ሮኬት ግን ማሽኑ ተገጥሞላት ከተፈለገው ቦታ ላይ እንድታርፍ ተደርጋለች ብለዋል። 

የሮኬት ማስወንጨፍ ሂደቱ ብዙዎችን ያስገረመ እንደነበርና ከአምስት ኪሎ ሜትር በላይ መወንጨፍ የሚችሉ ሮኬቶች በሳይንስ ማዕከሉ እየተፈጠሩ እንደሆነም ገልጸዋል።

ግንቦት ወር 2015 የተወነጨፈችው ሮኬት 43 ጫማ ገደማ መወንጨፏን አክለዋል። 

ዩንቨርሲቲው የአጼ ቴውድሮስን የእውቀት ጥያቄ የመመለስ ታሪካዊ ሃላፊነት አለበት ያሉት ፕሮፌሰር አዲሱ ተጨማሪ ለመስራት የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

አክለውም እስከ 2020 ድረስ ዩንቨርስቲው ሳተላይት የማምጠቅ እቅድ እንዳለው በመግለጽ፤ በጉና ተራራ ላይ የህዋ ምርምር ማዕከል ለመገንባት መታሰቡንም ተናግረዋል ።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *