ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ቴሌኮም ኩባንያ አዲስ ሀላፊ ሾሟል።
ላለፉት ሶስት ዓመታት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች እና ቁጥጥር ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለኢትዮ ነጋሪ እንዳረጋገጠው አምባሳደር ሔኖክ የቀድሞውን የድርጅቱ መሪ የነበሩት ማቲው ሀሪሰንን ተክተዋል።
አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ20 በላይ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በቅርቡም በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ እንደሚያገኝ ተገልጿል።