በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ከተገለጸ ስድስት ወራት ያስቆጠረ ሲሆን የሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከአምስት ሺህ 500 በላይ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸውም ተገለጿል ።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጀምሮ ከ5,500 በላይ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ ተጠቅተዋል ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ 118 ከፍተኛ ተጠቂ አካባቢዎች የለየ ሲሆን የወረርሽኙ ተጠቂዎች የሚታከሙባቸው 41 የኮሌራ ህክምና ማዕከላት ማቋቋሙን ገልጿል።
በዋናነት ችግሩ የታየባቸው አካባቢዎች የሶማሌ፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች፤ የኦሮሚያ፤ የአፋር፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ናቸውም ብሏል ።
አጣዳፊ ተቅማጥ የሚያስከትለው የኮሌራ ወረሽኝ የሚሰራጨው በተሐዋሲው የተበከለ ምግብ አልያም መጠጥ በመውሰድ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኦቻ አሳስቧል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በምኅጻሩ አተት ወይም አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በተደጋጋሚ የጤና እክል ሆኖ ይታያል፡፡