የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለአልዐይን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሮ ወይም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ህብረቱ በመግለጫው እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ለሰብዓው ድጋፎች የሚውል 60 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መስጠቱን ገልጿል፡፡

ህብረቱ አሁን ከለገሰው 22 ሚሊዮን ዩሮ ጋር በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የረዳው ገንዘብ መጠን 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይደርሳልም ብሏል፡፡

በኢትዮያ ባለፉት ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ እና መፈናቀል ምክንያቶች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እርዳታ ለማድረግ እንዳነሳሳውም አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሶማሊያ በግጭት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎችን ቁጥር 890 ሺህ ከፍ አድርጎታል ብሏል፡፡

በህብረቱ የቀውስ አስተዳድር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሊናርሲስ እንዳሉት “ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ተወስኗል” ብለዋል፡፡

“በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ባለሙያዎቻችን ሁኔታዎችን እየተከታተሉ ነው” ያሉት ኮሚሽነሯ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጎን መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *