ኢትዮጵያ የዩንቨርሲቲ ምሩቃንን ወደ ውጪ ሀገራት ልትልክ መሆኑን ገለጸች

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል

የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለመላክ አቅዶ 56 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጪ ሀገራል ልኬያለሁ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ መስሪያ ቤታቸው ያከናወናቸውን ስራዎች ለፓርላማው አብራርተዋል።

የሚኒስትሯን ሪፖርት ተከትሎ የፓርላማ አባላት “የውጭ ሀገር የስራ አማራጮችን ተጠቅሞ ለዜጎች ብቁ ስራ ዕድል ለመፍጠር ምን ታስቧል?” የሚል ጥያቄን አቅርበዋል።

በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አሰግድ ጌታቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የመዳረሻ ሀገራትን ለማበራከት ጥናት መጀመሩን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ እንደተያዘ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሴቶች በዩንቨርሲቲም ሆነ በኮሌጅ የተመረቁ፣ ቀደም ሲል ሰልጥነው ያልተሰማሩ እና የመሄድ ፍላጎት ያላቸው፣ የስደት ተመላሽ ሆነው ለመሄድ የሚፈልጉና የወንጀል መዝገብ የሌለባቸው እንዲሁም ስልጠና ወስደው የመሄድ ፍላጎት ላላቸው ነው ተብሏል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *