ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ምክንያት ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ሕይወቱን ማጥፋቱ የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።

በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ወጣቱ ለ2015 የትንሳኤ በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ያቀርባል።

ወላጆቹ ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉን ልቦሶች አጽድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቂነት ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቤተሰብ ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል።

በወላጆቹ እምቢታ የተበሳጨው ይህ ወጣቱ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ መለያየቱን ፖሊስ ገልጿል።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱን ተግባር አይፈጽምም የሚል እምነት እንደነበራቸው ተናግረዋል ።

ይሁንና ወጣቱ ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ እራሱን በገመድ ሰቅሎ ገድሏል ተብሏል።

የወጣቱ ድርጊት አድራጎት ቤተሰቡን ማስደንገጡና ማሳዘኑን ፖሊስ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *