southethiopia

ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ምክንያት ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ

ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ምክንያት ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ሕይወቱን ማጥፋቱ የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል። በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ወጣቱ ለ2015 የትንሳኤ በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ያቀርባል። ወላጆቹ ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉን ልቦሶች አጽድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቂነት ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቤተሰብ ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል። በወላጆቹ እምቢታ የተበሳጨው ይህ ወጣቱ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ መለያየቱን ፖሊስ ገልጿል። ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱን ተግባር አይፈጽምም የሚል እምነት እንደነበራቸው ተናግረዋል ። ይሁንና ወጣቱ ሚያዝያ 08 ቀን 2015…
Read More