በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳሩ ወደ አስቸጋሪ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የስነ መንግስት ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት የፓለቲካ ምዕራፍ እጅግ  አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርታ (ኢዜማ) ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ ገልፀዋል።

አቶ አበበ አካሉ ይሄን በእናት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እየገባ ነው።

በኢትዮጵያ እየተሸጋገረ የመጣውን አደገኛ የፓለቲካ ምዕራፍ በተበታተነ ትግል ውስጥ መቀልበስ እንደማይቻልም አቶ አንስተዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው የሚሉት አቶ አበበ ሰውነት እጅግ የረከሰበት ዘመን ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል።

አክለውም የአገር እሴት ሲናድ አብሮ የሚናድ አገረ መንግስት ምስረታ በመኖሩ የሀገርን ቋሚ እሴት’ና ምዕተ አመት ዘለል ተቋማት መከበር አለባቸው ብለዋል።

ምንም እንኳን እንደ ፓርቲ ህገመንግስቱ እንዲቀየር ስንታገል ብንቆይም አሁን ላይ እንደሀገር በደረስንበት አደገኛ ፓለቲካዊ ምዕራፍ አማካኝነት ህገ መንግስቱ እንዲከበር ለመጠየቅ ተገደናል ሲሉ አክለዋል።

አገር እንደ ሀገር አደጋ ላይ የወደቀችው በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ክፍተት ሲሆን ይሄውም የመንግስትነት ቁመናውን ህገ መንግስቱን ባለማክበሩ እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ባለመቻሉ እንደሆነ ተነስቷል።

ሰሞናዊ የአገሪቱን ጉዳይ በተለይ የአማራ ልዩ ሀይልን ትጥቅ ማስተፈታት ሂደት ተከትሎ የተስተዋለው ክስተት ጡንቻ መለካካት ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የገባንበት ቁርሾ ሳይለቀን ሌላ አደገኛ ምዕራፍ መክፈት መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ አፅንኦታቸውን ሰጥተዋል።

አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያካሂደው እናት ፓርቲ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

እናት ፓርቲ እያካሄደ ያለውን ጠቅላላ ጉባዔ ሊያደርግ የነበረው ከሳምንታት በፊት በወርሃ መጋቢት ነበር።

ይሁንና በወቅቱ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዳያካሂድ ተከልክሏል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ድርጊት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መኮነኑ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *