ሸራተን ሆቴል በጅማ ከተማ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ሊገነባ ነው

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ያለው ሸራተን ሆቴል በ ጅማ ከተማ በፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ደረጃ ባለ አምስት ኮከብ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል::

የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ አስቀምጠዋል፡፡

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ በፊት ጅማ ከተማ ኖክ ማደያ አካባቢ ለመገንባት አቅዶ የነበረውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ዘመናዊ ሆቴል ወደ ከተማዋ መግቢያ እንዲዛወር ተደርጓል።

ከዚህ በፊት ሆቴሉ ሊገነባበት የነበረው ቦታ ላይም ዘመናዊ የገበያ ማዕከል እንደሚገነባም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ኩባንያ አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ሰፊ ኢንቨስትመንት ካላቸው የግል ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቅሰው ድርጅቱ በክልሉ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጅማ ከተማ ላይ የሚገነባው ዘመናዊ ሆቴል 50 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን 120 አልጋዎች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የግራውንድ ቴንስ መጫወቻ እና ቅንጡ ማረፊያዎች ይኖሩታል።

ሆቴሉ የጅማን ባህል እና ወግ በሚያንፀባርቅ መልኩ እንደሚገነባም ተጠቁሟል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *