በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት ከ1ሺህ 300 በላይ ትዳር መፍረሱ ተገለጸ።

ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ከ1ሺህ 300 በላይ ትዳር በፍቺ መጠናቀቃቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ የተመዘገበው የፍቺ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ተቀራራቢ ሲሆን፤ በ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 623 የፍቺ ምዝገባዎች መደረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 16 ሺህ 35 ፍቺዎች እንደተካሄዱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ቤቴልሔም እንደሚገልጹት መረጃዎቹ የሚያመላክቱት በመስሪያ ቤቱ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡትን ብቻ ነው።

እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ በተለያዩ ቦታዎች በህጋዊም ሆነ በባህላዊ መልኩ ፍቺ እና ጋብቻ ይከናወናል፤ ነገር ግን ወደ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መተው የሚመዘገቡት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ናቸው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *