ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች።

የትምህርት እድሉ ከ5 አመታት በፊት የተጀመረው የ “ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል” ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው።

በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ6 ተማሪዎች የሶስተኛ ዲግሪ፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ ለ12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላርሺፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸዋል።

በአጠቃላይ የተሰጠው የትምህርት እድል 2 ነጥብ 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል።

የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደው ስነስርዓት ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች ተምረው አገራቸውንና ራሳቸውን መጥቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *