08
Apr
የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ከተመሰረተ በኃላ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ረዳ ምክትል በመሆንና የሰላምና ፀጥታ ካቢኔ ሲክሬተርያት ሀላፊ ብሎም የትግራይ ጦር አዛዥ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት ጀነራል ታደሰ በዛሬው እለት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሆነው ተሾመዋል። ጀነራል ታደሰ ቀደም ሲል በህወሓት አቶ ጌታቸውን በመተካት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ተመርጠው ፌደራል መንግስትም ይህንኑ የህወሓት ምርጫ ተቀብሎት እንደነበር ከዚህ ቀደም ፓርቲው ማስታወቁ አይዘነጋም። ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን የተረከቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና ሌሎች አካላት በስልጣን ርክክቡ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ጀነራል ታደሰ ወረደ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ፣ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መልሶ…