04
Feb
ለሁለት ዓመት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም ምክንያት የሆነው የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት አፈጻጸም የሚከታተል የባለሙያዎች ቡድን ትግራይ ክልል መቐለ መግባቱ ተገልጿል። ስምምነቱ እንዲፈረም ያደራደረው የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎችን ቡድን ያቋቋመው ከኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና አልጀሪያ የተውጣጡ ናቸው። ይህ የባለሙያዎች ቡድን በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታታቸውን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች መቀጠላቸውን፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የመከታተል ሀላፊነት ተሰጥቶታል። ዛሬ መቐለ መድረሱ የተገለጸው ይህ የባለሙያዎች ቡድን መቀመጫውን መቐለ በማድረግ የስምምነቱን አፈጻጸም ሲከታተል የቆየ ሲሆን ላለፉት ወራት በዕረፍት ላይ መቆየቱን የትግራይ ሰላምና ደህንነት ቢሮ አስታውቋል። ይህ የባለሙያዎች ቡድን ከአስተዳድራዊ ዕረፍት በኋላ ወደ መቐለ የተመለሰው በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ…