Polio

የፖሊዮ ቫይረስ በኢትዮጵያ ዳግሞ ማገርሸቱ ተነገረ

የፖሊዮ ቫይረስ በኢትዮጵያ ዳግሞ ማገርሸቱ ተነገረ

የፖሊዮ ቫይረስ በኢትዮጵያ እንደገና መከሰቱን ተከትሎ ከ11 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የሚያካትት የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻን ሊካሄድ ስለመሆኑ ተገልጿል። ቫይረሱ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በአምቦ አካባቢ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በደራሼና ጎፋ ዞኖች መከሰቱን የገለጸው የኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት ቫይረሱ ከዚህ ቀደምም በጋምቤላ ክልል በክልሉ ዋና ከተማ ጋምቤላ፣ በኑዌርና በኢታንግ ልዩ ወረዳዎች መከሰቱን አስታውቋል። ቫይረሱ በተከሰተባቸውና ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አምስት የሀገሪቱ ክልሎች የቤት ለቤት የክትባት ዘመቻ ይካሄዳል ያለም ሲሆንዘመቻው ከወርሀ ህዳር አጋማሽ ጀምሮ በሁለት የተለያዩ ዙሮች እንደሚካሄድ ገልጿል። በዘመቻው በ120 የአዲስ አበባ ወረዳዎች 884 ሺ 323፣ በ81 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወረዳዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገደማ፣ በ276…
Read More