28
Feb
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በኤርትራ ጉዳይ የሰጡት ሀሳብ የመንግስት አቋም አለመሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ሙላቱ (ዶ/ር) ኤርትራን አስመልክቶ ያጋሩት ጽሁፍ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንትት በፊት አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ግጭት እንዳይከፈት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተነሱትን ነጥቦች አጣጥለዋል። ስለ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጽሁፍ ኤርትራ ምላሽ የተጠየቁት አምባሳደር…