landmine

በትግራይ ክልል 259 ሰዎች በፈንጅ መገደላቸው ተገለጸ

በትግራይ ክልል 259 ሰዎች በፈንጅ መገደላቸው ተገለጸ

በትግራይ ክልል ባለፈው ሁለት አመት 1664 ሰዎች በተቀበሩ ፈንጂዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈፀመ ወዲህ ይህንን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከእነዚህ ውስጥ 259ኙ ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የክልሉ መልሶ ግንባታና ልማት ድርጅት (ራዶ) አስታውቋል፡፡ አለም አቀፍ የፈንጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቀሌ በተደረገ ስብሰባ ላይ የክልሉ መልሶ ግንባታና ልማት ድርጅት ሀላፊው አቶ ተስፋይ ገብረማሪያም እንደገለፁት የተቀበሩ ፈንጂዎችና ጥይቶች አሁንም በተለያዩ የትግራይ ክፍሎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የፈንጂ አምካኝ ግብረ ሀይል አስተባባሪ የሆኑት ኮሎኔል ተስፋይ አብርሀ በበኩላቸው በክልሉ ውስጥ በየቀኑ የፈንጂ አደጋዎች እየደረሱ መሆናቸውን ገልፀው የበጀት እጥረትና ለጉዳዩ በቂ ትኩረት አለመስጠት ስራቸውን እያደናቀፈባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ትግራይን…
Read More