Konjitsineggiorgis

አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንጋፋዋ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አምባሳደር  ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል። አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው። አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በአፍሪካ ህብረትና በተባባሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንም ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሰርተዋል። ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይም ልዩ አማካሪ ነበሩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአምባሳደር ቆንጂት ሕልፈትን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ  ኢትዮጵያ ዲፕሎማቷን እንዳጣች እና ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው…
Read More