11
Oct
ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጎን እንድትቆም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ጥሪ አቀረበ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ተቋማት፣ በሐማስ የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያወግዙ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ አሁን ስለጥቃቱም ይኹን ስለ ግጭቱ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡ ኾኖም፣ ኢትዮጵያ ገለልተኛ አቋም እንዳላትና ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ሃማስ በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን ሰለባ መሆናቸዉን በኢትዮጵያ እስራኤል ኤምባሲ አስታዉቋል፡፡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አደማሱ እንዳሉት በወቅታዊ የጉዳቱን መጠን አሁን ላይ መግለጽ ባይቻልም ከተጎጂዎች መካከል ግን ቤተ እስራኤላዊያንና ኢትዮጵያዉያን እንደሚኖሩ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ ከ1200 በላይ እስራኤላዉያን መሞታቸዉን አምባሳደር አለሊ…