Internetaccess

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ተባለች

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ተባለች

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ ላይ የታተመ አንድ የጥናት መጽሐፍ አመላከተ። “የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በብሪታንያ ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት ላይ በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል። በዚህም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል። በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንትርኔት የዘጋች በሚል ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል።…
Read More