29
Apr
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡ እቅዱ በገጠር ያሉ ዜጎች የሚፈልጓቸውን ምርቶች ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይጓዙ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡ በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት፤ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡ በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸውን የጠቀሰው ተቋሙ፤ ቁጥራቸውን ለማሳደግ እቀጥላለሁ ብሏል፡፡ በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ፤ የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳልም ተብሏል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ 151,000 ሰዎች በመካከለኛ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ…