fertilizercomplex

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስማማ

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስማማ

የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ማምረት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ በመድረሳችን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አለን!" ብለዋል። 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ሲሆን፤ "ይህም ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ ያደርጋታል" ብለዋል። "ፕሮጀክቱ በሀገር…
Read More