Ethiopiafootball

ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመቻል ተሸነፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመቻል ተሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። የመቻልን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጨዋች ከነዓን ማርክነህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ፈረሰኞቹ በዛሬው ጨዋታ ሙሸነፋቸውን ተከትሎ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል። የቀድሞው መከላከያ እግር ኳስ ክለብ የአሁኑ መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 33 በማድረስ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ51 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከተከታዩ ባህርዳር ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ጠቧል። በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም መቻል ከ ሲዳማ…
Read More
ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

በሳሙኤል አባተ በምድብ ለ ሀዋሳ ላይ እየተከናወነ በሚገኜው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሻሸመኔ ከነማ ቀሪ 4 ጨዋታ እያለው ወደ ቤቲኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል ። በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 24 አዲስ አበባ ከነማ በቦዲቲ ከነማ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ሻሸመኔ ቀሪ 4 ጨዋታዎች እያሉት በ 47 ነጥብ ፕሪሜር ሊጉን ተቀላቅሏል ። አዲስ አበባ ከነማ በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በቀጣይ ቀሪ 2 ክለቦች ሊጉን ይቀላቀላሉ ። በምድብ ሐ  ሀምበርቾ ዱራሜ በ 42 ነጥብ ገላን ከተማ በ 40 ነጥብ የምድቡ አንደኛ ሁኖ ለማለፍ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ። በተመሳሳይ በምድብ ሀ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 50 ነጥብ ምድቡን ሲመራ ቤንቺ ማጅ በ…
Read More
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሰሞኑ የስራ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስገባታቸው ሲገለጽ ነበር። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረገጹ እንደገለጸው ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት መለያየቱን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ከአሰልጣኙ የቀረበለትን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ ማጽደቁን ገልጾ አሰልጣኙ እስካሁን ላደረጉት ስራ ምስጋናውን አቅርቧል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጊኒ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል። የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የግብጽ ብሔራዊ ቡድንን 2 ለ 0 ማሸነፋቸውን ተከትሎ…
Read More
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል። የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል። የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ…
Read More