Emergency

በአዲሱ የነዳጅ አቅርቦት መመሪያ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው?

በአዲሱ የነዳጅ አቅርቦት መመሪያ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው እነማን ናቸው?

የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን በመካከለኛው ምስራቅ ያጋጠመውን ጦርነት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመቋቋም በአገር ውስጥ የነዳጅ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚያዝ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። በመመሪያው መሠረት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ለማንኛውም የነዳጅ ዓይነት አቅርቦት ቅድሚያ እንዲሰጡ ያላቸውን አካላት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ለፀጥታ ተቋማት፣ ቁልፍ ለሆኑ የመንግስት ፕሮጀክቶች እና በተለይም በመጠናቀቅ ላይ ላሉ የልማት ስራዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው አዟል። ለኢንዱስትሪዎች፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ለሚያመርቱ አምራች ድርጅቶች እና ምርታቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ ተቋማትም ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ከተባሉ አካላት መካከል ናቸው። እንዲሁም ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለሚታይባቸው እና የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት ፍሰት ላለባቸው የኮሪደር አካባቢዎች እና ለሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች…
Read More