12
Sep
በአሜሪካ ሀገር የሚገነውና በሕዋ ሳይንስ ምርምር ላይ የሚሰራው 'ታይታንስ ስፔስ ኢንዱስትሪ' በ2029 ወደጠፈር ለሚያደርገው ጉዞ ኢትዮጵያዊቷን እመቤት መሀባውን ከተጓዥ ተመራማሪዎች መካከል አንዷ እንድትሆን መርጧታል፡፡ እመቤት መሀባው ከልጅነቷ አንስቶ ለሕዋ ሳይንስ ፍቅር እንደነበራት የተገለጸች ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በሕዋ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ስኮላርሺፕ አግኝታ ወደሕንድ አቅንታለች። በኋላም አሜሪካ ውስጥ በሕዋ ሳይንስ ምርምር ላይ የሚሰራውን ታይታንስ ስፔስ ኢንዱስትሪን መቀላቀሏን ተከትሎ፤ በተቋሙ በኤሮስፔስ ኢንጂነርነት ሙያዋ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነች ይገኛል። የምትሰራበት የሕዋ ምርምር ተቋም በእ.አ.አ. በ2029 ወደጠፈር ለሚያደርገው ጉዞ እመቤት መሀባውን ከተጓዥ ተመራማሪዎች መካከል አንዷ እንድትሆን መርጧታል። ለዚህ ምርጫ የተለያዩ መስፈርቶች ቢኖሩትም፤ ግዳጁን ለመፈፀም በአካል፣ በስነልቦናም ሆነ በምርምር…