edif

የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር አረቦን ሰበሰበ

የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር አረቦን ሰበሰበ

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 08 ቢሊዮን አረቦን ብር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ገለጸ። መድን ፈንዱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 2 ነጥብ 08 ቢሊዮን አረቦን ብር እንደሰበሰበና ይህም ከታቀደው እቅድ አንጻር መቶ በመቶ ተፈጻሚ ሆኗል። ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲታይም የ27 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የተሰበሰበው አረቦን ብር ሊያድግ የቻለው የአባል ፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ ገንዘብ በማደጉ ምክንያት እንደሆነም ተጠቅሷል። በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ብር 9 ነጥብ 56 ቢሊዮን ከአባል ፋይናንስ ተቋማት ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝና ይህም ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30 ነጥብ 25 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን…
Read More