13
Oct
በአፋር ክልል፣ ኪልበቲ ረሱ ዞን፣ በርሃሌ ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ 43,456 ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሁሴን እንዳሉት ለተፈናቃዮቹ የሚሆን ምግብ እና መጠለያ፤ ከባድ ጉዳት ወደ ደረሰባቸው ቀበሌዎች እየተጓጓዘ ነው ብለዋል። በክልሉ ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከበርሃሌ በተጨማሪ በተመሳሳይ ዞን ውስጥ በሚገኙት ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎችም የተከሰተ እንደነበርም የክሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። በበርሃሌ ወረዳ የመጀመሪያው ርዕደ መሬት ከደረሰበት ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ለስድስት ጊዜያት ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አቶ አሊ አስረድተዋል። በወረዳው ካሉ ቀበሌዎች በርዕደ መሬቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው፤…