05
Mar
በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የኮንዶም እጥረት ለመቅረፍ የግል የመድሃኒት አስመጪዎች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡ በየዓመቱ በመንግስትና በግብረሰናይ ድርጅቶች ከ90 ሚሊዮን ያልዘለለ አቅርቦት ቢኖርም ዓመታዊ ፍላጎቱ ግን 270 ሚሊዮን ይደርሳል፤ ቀድሞውንም ቢሆን እጅግ የተራራቀ አቅርቦትና ፍላጎት ያለበት ኮንዶም አሁን ደግሞ የአሜሪካ መንግስት የተራድኦ ድርጅት የሆነው ዩኤስ አይዲ የሚሰጠውን ድጋፍ ማገዱ እጥረቱን አባብሶታል፡፡ ከዚህ ቀደም በነፃ ይታደል የነበረው፣አልፎ አልፎም በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በየሱቁ ይገኝ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የአንድ ኮንዶም አማካኝ ዋጋው 50 ብር ደርሷል፡፡ እንደ ጋምቤላ ባሉ የክልል ከተሞች እጥረቱን ተከትሎ በተፈጠረ የዋጋ ንረት አንድ ኮንዶም እስከ 250 ብር እተሸጠ መሆኑን ተነግሯል፡፡ በዚህና በሌላውም ምክንያት ኮንዶምን የመጠቀም ዝንባሌ መቀነስ…