03
Nov
አዋጭ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አሰራሩን ያሻሻሉ አዳዲስ ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል። ተቋሙ የቁጠባ ጊዜን ከ6 ወራት ወደ 3 ወራት ዝቅ ማድረጉን ሲገልጽ የሚሰጠውን የብድር ጣሪያውን ደግሞ እስከ 25 ሚሊዮን ብር ማሳደጉን አስታውቋል። እንዲሁም የመኪና ብድር ለመስጠት ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የቁጠባ መጠኑ ደግሞ ከ40% ወደ 25% ቀንሷል። አዋጭ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (ሳኮስ) የአባላቱን የፋይናንስ ፍላጎት በተሻለ ለማሟላትና የማኅበረሰቡን የኑሮ ጫና በተጨባጭ ለማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የቁጠባና ብድር ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታውቋል። ማሻሻያውን አስመልክቶ የአዋጭ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ላለፉት 20 ዓመታት አባላቱን በኢኮኖሚ በማጠናከርና ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት…