ኢሕአፓ

ኢሕአፓ ከሀገራዊ ምክክሩ ራሱን አገለለ

ኢሕአፓ ከሀገራዊ ምክክሩ ራሱን አገለለ

ኢሕአፓ ያስቀመጣቸው ቅድመሁኔታዎች እስከሚሟሉ ድረስ ከዛሬ ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ እራሱን ከሀገራዊ ምክክሩ ያገለለ መሆኑን አስታወቋል። ኢሕአፓ ኮሚሽኑ ሲመሠረት ከነበረው እውነታ ባሻገር የተፈጠሩ ግጭቶችን ለሀገራችን ቀውስም ወሳኝ ቦታ ያላቸው ሁኔታዎችን ለማካታት የሚያስችል ተልዕኮም ይሁን ህጋዊ ማዕቀፍ አለመኖሩ አሁን እየተካሄደ ባለበት መልኩ የኮሚሽኑ የሥራ ውጤት በአገራችን ውስጥ ዘላቂ ሰላምን ያመጣል ብሎ እንደማያምን ገልጿል። ኢሕአፓ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፉ የመጡትን ቀውሶች በአገራዊ በቅንነት ምናልባት በድርድርና ምክክር ሊፈቱ ይችሉ ይሆናል በሚል ተስፋ ለተወሰኑ ዐመቶች ሲሳተፍባቸው የቆየ መሆኑን በመግለጽ ''ገዥዎቻችን ችግሮችን በቅንነትና በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ አገራዊ ምክክርና መግባባትን የራሳቸውን ሥልጣን ማጠናከሪያና የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ ማደናገሪያ'' አድርገው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል ብሏል። አሁን…
Read More