አዋጭ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አሰራሩን ያሻሻሉ አዳዲስ ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል።
ተቋሙ የቁጠባ ጊዜን ከ6 ወራት ወደ 3 ወራት ዝቅ ማድረጉን ሲገልጽ የሚሰጠውን የብድር ጣሪያውን ደግሞ እስከ 25 ሚሊዮን ብር ማሳደጉን አስታውቋል።
እንዲሁም የመኪና ብድር ለመስጠት ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የቁጠባ መጠኑ ደግሞ ከ40% ወደ 25% ቀንሷል።
አዋጭ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (ሳኮስ) የአባላቱን የፋይናንስ ፍላጎት በተሻለ ለማሟላትና የማኅበረሰቡን የኑሮ ጫና በተጨባጭ ለማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የቁጠባና ብድር ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታውቋል።
ማሻሻያውን አስመልክቶ የአዋጭ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ላለፉት 20 ዓመታት አባላቱን በኢኮኖሚ በማጠናከርና ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።
አዲሱ ማሻሻያም ወቅታዊውን የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የሀገሪቱን የኅብረት ሥራ ሕጎችና ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ መርሆዎችን መሠረት ያደረገ ነው ያሉት አቶ ዘሪሁን በማሻሻያው መሠረት አባላት የመግዛትና ኢንቨስት የማድረግ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የብድር ወለድ አባላት ከተበደሩት ገንዘብ 75 በመቶ ላይ ብቻ እንዲታሰብ መወሰኑንም ገልጸዋል።
አቶ ዘሪሁን የአዋጭ አባል መሆን ቆጥቦ ከመበደር ባሻገር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ባለቤት እንደሚያደርግ ጠቅሰው፣ መላው ማኅበረሰብ፣ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች፣ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በመገኘት አባል በመሆንና የማሻሻያውን ሙሉ መረጃ በመጠየቅ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።