ኢትዮጵያ የ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ በፋዊ ጥያቄ አቀረበች

​ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ውድድር ለማስተናገድ ይፋዊ የጨረታ ጥያቄዋን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ማቅረቧን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ሀገሪቱ ውድድሩን ለመጨረሻ ጊዜ ያዘጋጀችው በ1976 እንደመሆኑ መጠን፣ ጥያቄው ከተቀባይነት ካገኘ ከ50 ዓመታት በላይ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቁን አህጉራዊ መድረክ ዳግም ይመልሳል።

​የ2028ቱ ውድድር ከአፍሪካ ዋንጫ የተለመደ ባለሁለት ዓመት ዑደት ተለውጦ በየአራት ዓመቱ መካሄድ የሚጀምርበት የመጀመሪያው ውድድር ይሆናል።

130 ሚሊዮን ሕዝብና የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ዝግጁነቷን ብታረጋግጥም፣ በባህር ዳር እና በመዲናዋ የሚከናወኑ የስቴዲየም ግንባታዎች እንዲሁም የጸጥታ ስጋቶች በዝግጅት ሂደቱ ላይ የሚጠበቁ ተፎካካሪ ተደራራቢ ፈተናዎች ናቸው።

​በፊፋ ደረጃ 143ኛ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ እ.ኤ.አ. በ2027 ጎረቤቶቿ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ የሚያዘጋጁትን ውድድር ተከትሎ አህጉራዊውን ድምቀት ወደ ምስራቅ አፍሪካ የመመለስ ትልቅ ተስፋን ሰንቃለች።

ኢትዮጵያ የካፍ እና ፊፋ እውቅና ያለው ስታዲየም ባለቤት ባለመሆኗ ብሔራዊ ቡድኑን ጨምሮ ክለቦች በውሰት ሜዳዎች ሲጫወቱ ቆይተዋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የአዲስ አበባ እና የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም  መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል።

ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቶ አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላቱ ከሁለት ሳምንት በፊት የጥራት ማረጋገጫ መስጠቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የካፍ መስራች ሀገር ብትሆንም የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ሳታሟላ ቆይታ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ሳታዘጋጅ ቆይታለች።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለስፖርት መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከስታንዳርድ በታች የሆኑ ስታዲየሞቿን ደረጃ እያሻሻለች ትገኛለች።

የ2028 ካፍ እግር ኳስ ውድድርን ለማዘጋጀት ፍላጎቷን የገለጸች ሲሆን ከሎሎች ሀገራት ጋርም እየተፎካከረች ትገኛለች።

በአዲስ አበባም 62 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችል አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታ በማካሄድ ላይ ስትሆን ግንባታው በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *