የቀድሞው ልማት ባንክ እና አማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው በኪሳራ ላይ ላለው ጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾመዋል።
የአማራ ብድርና ቁጠባ ድርጅት በሚል ሲጠራ የነበረው በኋላም ጸደይ ባንክ በሚል ስያሜ የኢትዮጵያን የባንክ ቢዝነስ የተቀላቀለው ጸደይ ባንክ በኪሳራ ላይ ይገኛል።
ባንኩ በ2024/25 በጀት ዓመት ብቻ የሁለት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ከአንድ ወር በፊት ዓመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ ገልጿል።
ይህን ተከትሎም ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የባንኩ አዲስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሾሙለት ባንኩ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስታውቋል።
በኪሳራ ላይ ያሉ የገንዘብ ድርጅቶችን በመታደግ የሚታወቁት ዶክተር ዮሀንስ ከዚህ በፊት ልማት ባንክን እንዲሁም የአማራ ባንክን ከኪሳራ ወደ ትርፍ መመለሳቸው ይገለጿል።
ላለፉት ዓመታት ጸደይ ባንክን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የነበሩት መኮንን ማንያዘዋል ሀላፊነታቸውን ለቀዋል።
ጸደይ ባንክ የአመራር ችግር፣ የሰራተኞች አለመረጋጋት፣ በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ያስከተለው የኢኮኖሚ መቀዛቀስ እና የባንክ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ካሉበት ችግሮች መካከል እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል።
የክፉ ቀኑን መሪ ያጣው አማራ ባንክ እስካሁን በፕሬዝዳንትነት ማንን እንደሾመ አልገለጸም።