ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪአይፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መወሰኑ ተገልጿል።
ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሽልማት ያገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮች በቪ.አይ.ፒ ኤርፖርት እንዲስተናገዱ መንግሥት መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ትናግረዋል።
ላለፉት አራት አመታት በታማኝነት ፕላቲኒየም ሽልማት ያገኙ 30 ልዩ ተሸላሚዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ከሆኑ፤ የድርጅት ባለቤቶች ወይም ሥራ አስኪያጆች ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንደሚሰጣቸውም ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው 7ኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና መርሃ ግብር በትናንትናው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ሲሆን በመርሃ ግብሩ 700 የሚደርሱ ተቋማት እና አልሚ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚህም 105 የሚሆኑት በፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 በወርቅ ደረጃ የተቀሩት 350 የሚሆኑት ደግሞ በብር ደረጃ ዕውቅና ያገኙ ናቸው ተሰጥቷቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ላለፉት አራት ዓመታት በታማኝነት ፕላቲኒየም ሽልማት ያገኙ 30 ልዩ ተሸላሚዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ከሆኑ፤ ለድርጅት ባለቤቶች ወይም ሥራ አስኪያጆች ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የሚሰጣቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።
ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት በሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለስራ እንዲህ ዓይነት ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ቪዛን ጨምሮ ላለው ማንኛውም ነገር መስተጓጎል እንዳይገጥማቸው መሆኑንም ጠቅላይ ሚንስትሩ አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ ከግብር የምታገኘው ገቢ በየዓመቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባሳለፍነው በጀት ዓመት ውስጥ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ሰብስባለች፡፡
እንዲሁም በተያዘው ዓመት ደግሞ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ያቀደች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 900 ቢሊዮን ብሩ ከፌደራል መንግስት ከክልሎች ደግሞ 600 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡