ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ተጀመረ

አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታውቋል።

ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የድርጅቱ ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ ነው የምናስከፍለው። ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ወይም 16 ሺህ ብር ገደማ ያስከፍላል ተብሏል።

ከኛ በፊት ‘ሮያል አላይድ’ የተሰኘ ከናይሮቢ ሞያሌ እና ሞምባሳ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማራ ድርጅት አለ። ከአራት ዓመታት በፊት የተመሠረተው ‘ሮያል አላይድ’ እስከ ሞያሌ ከተማ ብቻ ይሠራ ነበር።

በአውሮፕላን ቲኬት መወደድ ሳቢያ የአውቶብስ ትራንስፖርት ፍላጎት መኖሩን እና ይህንን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል አገልግሎት አቅራቢ አለመኖሩን በጊዜው እንደ ችግር ይታይ ነበር።

ይህን ክፍተት ለመሙላት በሚልም አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች ቀጥታ ከናይሮቢ- አዲስ አበባ ጉዞ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል።

ድርጅቱ አሁን ላይ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በስምንት አውቶቡስ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን በቀጣይ በ16 አውቶቡሶች አገልግሎት የመስጠት እቅድ አለው ተብሏል፡፡

በየቀኑ ወደ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ መካከል የሕዝብ ማመላለስ ሥራዎችን የመስራት እቅድ እንዳለውም ተገልጿል።

ከዕሁድ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮም 7 ተሳፋሪዎች ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ያመጣ ሲሆን የመጀመሪያው ጉዞ ለሙከራ እና ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በነገው ዕለትም ሐሙስ ነሀሴ 1 ቀን 2017 ዓም ከናይሮቢ አዲስ አበባ ሁሉም ቲኬቶች ተሸጠው አልቋል ተብሏል፡፡

አውቶብሱ 46 ሰዎችን ብቻ እንዲጭን የተደረገበት ምክንያት ወንበሮች መካከል ክፍተት እንዲኖር እና ሰፋፊ ወንበሮችን ለመጠቀም እንደሆነ ተገልጿል።

አውቶብሶቹ ፦- አስተናጋጆች፣ – ራሳቸውን የቻሉ የሴቶችን እና የወንዶች መጸዳጃ፣- በውስጣቸው የኢንተርኔት እና ስክሪንን ጨምሮ የመዝናኛ አግልግሎት አላቸው ተብሏል።

የጉዞ መስመር እና ሰዓትን በተመለከተ አውቶብሱ ከቀኑ 10 ሰዓት ከናይሮቢ የሚነሳ ሲሆን፣ በማግስቱ ጠዋት ሞያሌ ይደርሳል።

ኢሚግሬሽን እስከሚከፈት ተሳፋሪዎች ያርፋሉ። ኢሚግሬሽን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ያልቃል። ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ከሞያሌ፤ በያቤሎ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዲላ፣ ሐዋሳ አድርጎ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ አዲስ አበባ ይገባል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *