የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችው ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት።
ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል።
በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሀፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች።
አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች።
መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ተናግራለች።
ለጊዜው ”Dissecting Haile’ በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።
መፅሀፉ ከመጭው ነሀሴ ወር ጀምሮ ለገበያ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
የአትሌት ኃይሌን የህይወት ታሪክ የሚመለከት ሌላ መፃህፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኗንም ልጁ ተናግራለች።
ሀይሌ ገብረስላሴ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ስኬታማ አትሌቶች መካከል ዋነኛው ሲሆኑ በበርካታ የዓለማችን ውድድሮችን አሸንፏል።
አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ከስፖርት በተጨማሪም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ስኬታማ ሆኗል።
ታላቁ ሩጫን በኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በፊት የመሰረተው አትሌት ሀይሌ ይህ ውድድር በየዓመቱ የሚካሄድ ተጠባቂ የአትሌቲክስ ውድድር ሆኗል።