የሆላንድ ዴይሪ የወተት ምርት አዲስ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን ገልጿል።
የሆላንድ ዴይሪ የሙዝ እርጎ አመጣጥ የኢትዮጵያውያን ሸማቾች ጣዕምን የሚያሟላ የወተት ተዋጽእዎችን ማቅረብ ላይ በማተኮር፣ የክሬም ይዘት ያለው ከተፈጥሯዊ የሙዝ ፍሬ ጣፋጭነት ጋር በማዋሃድ የሀገሪቱን የወተት ምርታማነት መስፈርት በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል ተብሏል።
ይህ አዲስ የሙዝ እርጎ ምርት አሁን ያለውን የስትሮውበሪ (ኢንጆሪ) እና የማንጎ እርጎ አቀራረብ አይነት በሚገባ እንደሚያሟላም ኩባንያው አስታውቋል።
ይህም የተቋሙን አቅርቦት በሌላ ከፍተኛ ጥራት ባለው ምርት በማሳደግ በሀገር ውስጥ ምርቱ በንቃት እንዲስፋፋ ያደርጋል ነው የተባለው።
የሆላንድ ዴይሪ የወተት ተዋጽኦዎችን ለማቅረብ ከ4ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል።
ሆላንድ ዴይሪ የደች ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኢትዮጵየዊያን እየተንቀሳቀሰ ያለ የንግድ ኩባንያ ሲሆን በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሆላንድ ዴይሪ ወተት፣ ቅቤ፣ ቺዝ፣ ችፕስ እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር እና በማሸግ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ድርጅትም ነው፡፡