የጥላቻ ንግግሮች የኢትዮጲያ ሴቶችን ከማህበራዊ ተሳትፎ እየገደበ ነው ተባለ

ኢትዮጲያ ውስጥ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከማህበራዊ ኑሮ እየተገለሉ እና በማህበራዊ ትሥሥር ድረ-ገፆች ላይም በተደጋጋሚ መገፋት እና ማጥላላት እየደረሰባቸዉ ነዉ።

እነዚህ ግኝቶች ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪዚሊየንስ (ሲ.አይ.አር) በተባለ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን፣ የሀሰት መረጃን እና ኢንተርኔት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከላከል ላይ አተኩሮ በሚሰራ ገለልተኛና ለትርፍ ባልተቋቋመ ተቋም በተደረጉ ጥናቶች የተገኙ ናቸው።

ይህ ጥናት ሲ.አይ.አር ኢትዮጲያ ውስጥ በፌስቡክ፣ ኤክስ (X) እና ቴሌግራም ላይ የሚፈጸሙ ጾታን መሰረት ያደረጉ ትንኮሳዎች ላይ ቀደም ብሎ ያደረገውን ጥናት ወደ ሁለት ተጫማሪ የማህበራዊ ትሥሥር ድረ-ገፆች ማለትም ዩትዩብና ቲክቶክ አስፋፍቷል።

ግኝቶቹም እንደሚያሳዩት በማህበራዊ ትሥሥር ድረገፆች ላይ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች የሰዎችን የመናገር፣ የመምራት እና በዲጂታሉ አለም ያላቸውን ደህንነት እየገደበ እንዳለና እና በዚህም ምክንያት ኢትዮጲያዊ ሴቶች ወደ ዳር እየተገፉ መሆኑን ነው። ሲ.አይ.አር በሴቶች ማንነት እና ክብር ላይ የተስፋፉ ጥቃቶች ፣ የሴቶችን የበታችነት የሚጠቁሙ መልዕክቶች እና ክብር-ነክ የሆኑ የጅምላ አመለካከቶች መኖራቸውን ተመልክቷል።

የተለመደውን የአኗኗር ዘይቤ የሚቃወሙ ሴቶች፤ በአመራር ሚና ወይም በሴቶች ስፖርት ውስጥ ያሉ ሴቶችን በወሲባዊ ምልከታ እንዲታዩና ዝቅተኛ ግምት እንዲሰጣቸው ሆነዋል፣ መገለል እና መኮነንም ደርሶባቸዋል። ነገር ግን የጥላቻ ንግግሮች ተፅእኖ ከግለሰብ ጉዳቱ የዘለለ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ሴቶች በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያዳክምና የሚገድብ ነው፡፡

ይህ ጥናት በምሁራን በተገመገመ የጥናት ዘዴና በሲ.አይ.አር የታተሙ 2058 ጥላቻ አዘል ቃላት ላይ በመመርኮዝ ተፅዕኖ ፈጣሪና ተደማጭ በሆኑ የዩትዩብና ቲክቶክ ገፆች ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን በአራት ቋንቋ ማለትም አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛና እንግሊዝኛ አጥንቷል።

ጥናቱ በኢትዮጲያ የጥላቻ ንግግር ትርጓሜ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ይህም ማለት ብሄር፣ ሃይማኖት፣ ዘር፣ ፆታ እና አካል ጉዳተኝነት ተካተዋል። በአውደ-ጥናት መድረኮች እና በስብሰባዎች ላይ የተገኙ ጥቃት የደረሰባችዉ ግለሰቦች፤ በሴቶች እና ልጃገረዶች መብቶች፣ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት እና በበይነ መረብ ደህነነት ላይ አትኩረዉ የሚሰሩ የዘርፉ ባለሞያዎችም በግኝቶቹ ላይ አስፈላጊ አውድ እና ሞያዊ አስተያየታቸውን አበርክተዋል።

መርማሪዎች በሴቶች ላይ የሚደርሱት ጥቃቶች በስርዓተ ፆታ ዙሪያ የተሳሳቱ አመለካከቶችን የያዙና በማህበራዊ ሚናቸው ዙሪያ ያጠነጠኑ መሆናቸውን ገልጽዋል።

ጥናቱ በተጨማሪም በተደራራቢ ጥቃቶች ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙ አዝማሚያ በማሳየት ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በፆታቸው ብቻ አለመሆኑን አሳይቷል። ፖለቲካዊ ሁነቶች እና ውስጣዊ ግጭቶች ብሄር ተኮር ጾታዊ የጥላቻ ንግግሮችን ያፋፍማሉ፣ በተመሳሳይ ሀይማኖታዊ ተጽእኖዎች አብዛኞቹ ሴቶችን ለማጣጣል እና ለማጠልሸት የሚውሉ ንግግሮች ሆነው ተገኝተዋል። ጥናቱ የስርዓተ-ፆታ ሚናዎች የወንዶችንም ንቁ የኢንተርኔት ላይ ተሳትፎና እንቅስቃሴ እንደሚገድቡ www.info-res.org አሳይቷል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያሉ ሴቶችና እና ወንዶች የሚጋፈጡት ጥቃቶች በአይነት የተለያዩ ናቸው፣ ሴቶች ይናቃሉ፣ ይገለላሉ፣ መሳለቅያም ይሆናሉ።

በአንጻሩ ውንዶች ደካማ በመባል፣ ወንዳወንድ ባለመሆን ወይም የጾታ እኩልነትን በመደገፋቸው ይጠቃሉ። በተለይም ተመራማሪዎች እንደደረሱበት ወንዶች ሌሎችን ወንዶችን ሆነ ሴቶችን ለመስደብ የሴቶችን የሰውነት አካል እንደመሳሪያ ይጠቀማሉ፤ በዚህም ሴቶች በይበልጥ ይገለላሉ። በዚህም የተነሳ ሴቶች ግንባር ቀደም የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ከመሆናቸውም ባሻገር የጥቃቱ ኢላማም መሳሪያና ተምሳሌትም ተደርገዋል፡፡

በአጠቃላይ ዩትዩብ ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው የጥላቻ ንግግሮች በበለጠ ሲታዩ ጉልህ የጥላቻ ንግግሮችና ሴቶችን እንደቁስ የሚቆጥሩ ንግግሮች በቲክቶክ ላይ እንደሚታዩ ሲ.አይ.አር ተመልክቷል።

ይህ ጥናት ይፋ እንዳደረገዉ አሁን ያሉት የይዘት ቁጥጥር አሰራሮች ሴቶች እና ልጃገረዶችን ኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች አንጻር ደህንነታቸውን በበቂ ደረጃ ለመጠበቅ እንደማያስችሉ ነው።

የአውደጥናቱ ተሳታፊዎች እንደ ኤክስ (X) እና ሜታ ባሉ ድረ-ገፆች በቅርቡ ከተደረጉ የይዘት መቆጣጠሪያ ፖሊሲ ለውጥ ጋር በተያያዘ ድረ-ገፆች በይበልጥ ተቃርኖዎች የሚስተዋሉባቸው እና ለተሳሳቱ እና ለተዛቡ መረጃዎች መስፋፋት በበለጠ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ያላቸውን ስጋት ገለጸዋል።

ሲ.አይ.አር በምርምር፣ በአውደ ጥናት እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ ግንቦት 2016 በተደረገ ኮንፍረንስ አማካኝነት እነዚህን ጉዳዮች ለመረዳት እና መፍትሄ ለመሰጠት ሲሰራ ቆይቷል።

በሌሎች መድረኮች እንደተከናወኑት ቀደምት ጥናቶች፤ በቲክቶክ እና ዩትዩብ ላይ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ተጫባጭ የሆነ መዘዞች ስላሏቸው የኢንተርኔት ላይ አለም ከትክክለኛው አለም የተለየ ነው የሚሉ ግትር እና የተሳሳቱ አመለካከቶች መቀልበስ አላባቸው።

“በኢንተርኔት ላይ የሚፈጠሩ ክስተቶች በኢንተርኔት ላይ ብቻ አይቀሩም። ኢትዮጲያ ውስጥ በማህበራዊ ትሥሥር ድረ-ገፆች ላይ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች አደገኛ ውጤቶችን አስከትለዋል። በተለይም በትግራይ ጦርነት ውቅት እንደተመለከትነው የሰዎችን የግል መረጃን በኢንተርኔት ላይ በማስፍር በእውነተኛው ዓለም ላይ ጥቃቶችን እና ሞትንም ጭምር አስከትሏል” ሲሉ የሲ.አይ.አር የምርምር ሃላፊ ፌልሲቲ ሙልፎርድ ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *