የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡

60 ሚሊየን ዶላር በነገው ዕለት በሁሉም ባንኮች ለጨረታ እንደሚቀርብ ባንኩ አስታውቋል።

ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራምን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ክፍያ ሚዛን በተለይም የወጪ ንግድ፣ ሐዋላና የካፒታል ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል ማሳየቱን ጠቅሷል።

በተለይም ከቅርብ ወራት ወዲህ ወርቅን ወደ ውጭ የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ላለው ብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በመጨመሩ ምክንያት የባንኩ ዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መጨመሩን ገልጿል።

በመሆኑም ከባንኩ የወርቅ ግዥ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ለማገናዘብና በማዕከላዊ ባንኩ እጅ ካለው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከፊሉን ለግሉ ዘርፍ በመስጠት በገበያው ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል ባንኩ የተወሰነ የውጭ ምንዛሪ ለባንኮች በጨረታ ለመሸጥ መወሰኑን አስታውቋል።

ባንኮችም በተቀመጠው መስፈርት እና የጊዜ ማዕቀፍ መሰረት በጨረታው እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያ እንዲመራ የወሰነች ሲሆን አሁን ለይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር በባንኮች እንዲሁም 140 ብር ደግሞ በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ስራ የጀመረው ገዳ ባንክ ጨረታውን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *