ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የዲጂታል ጉብኝት እያደረጉ ነው

ሶስት ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሁዋዌ አዘጋጅነት ለስምንት ቀናት በሚቆይ የዲጂታል ጉብኝት እየተሳተፉ ሲሆን ጉብኝቱ በቻይና ሼንዘን ተጀምሮ ቤጂንግ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ለተመረጡ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ “Huawei Seeds for the Future (SFTF) Tech 4 Good” ያለፈው ዓመት ሰልጣኞች የተዘጋጀው ጉብኝቱ ነሐሴ 26 ተጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል።

ጉብኝቱ ለተማሪዎች የቻይናን ዲጂታል መልከዓ ምድር ለመቃኘት፣ የአይሲቲ ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ጅምሮችን ለማዳበር፣ እንዲሁም ተማሪዎቹ ስለሚሰሯቸው ስራዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ከኢንዱስትሪ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት እንዲያደርጉ ልዩ እድል ይሰጣል።

ተማሪዎች በዚህ ስልጠና እንዲሳተፉ ለማድረግ የማጣራት ሂደትን ያለፉ ሲሆን ከ2023 የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ውስጥ ምርጥ ተሳታፊ ከነበሩት ውስጥ 5% ተማሪዎችን በመጋበዝ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደ የአይሲቲ ግንዛቤ፣ የወጣቶች ስራ ፈጣሪነት እና ዘላቂነት እንዲሁም በግል የእድገት እቅዳቸው እና የስራ አላማዎቻቸው ላይ ቪዲዮ ሰርተው እንዲያቀርቡ በማድረግ ተወዳድረዋል። በመጨረሻም ሶስት ተማሪዎች የቻይና ጉብኝት እድሉ ተሰጥቷቸዋል።

በጉብኝቱ እየተሳተፉ ያሉት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉብኝቱ የዲጂታል አለም አሰራርን በተመለከተ ጥልቅ ግንዛቤ የማግኘትና ልምድ የመቅሰም እድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

ጉብኝቱ የተለያዩ ሁነቶችን የሚያስተናግድ ሲሆን በሁዋዌ ዶንግጓን ካምፓስ ጉብኝት የስማርት ፒቪ ማሳያ፣ የአይሲቲ ልዩ ኮርሶች የሚታዩበት የሁዋዌ ኤግዚቢሽን አዳራሽ ጉብኝት፣ የባህል ትስስርና የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች አሰራር፣ የሁዋዌ ዩኒቨርሲቲ እና የአርተፊሽያል ኢንተለጀንስ ዎርክሾፕ ጉብኝቶችን ያካተተ ሲሆን የዲጂታል ቴክኖሎጂን የሚያበረታታ የአፍሪካ እና የቻይና ወጣቶች ልማት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትንም ይዟል።

በ2024 የቻይና ዲጂታል ጉብኝት ላይ በሰሜናዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ ክልሎች የሚገኙ 17 ሀገራት የተውጣጡ 45 የተመረጡ ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ሁዋዌ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸውና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ ነው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *