አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መርጦታል፡፡

የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል።

ኢኤስፒኤን አህጉሪቱ ካላት ስፋት እና የስፖርት ብዛት አንጻር 25 ምርጥ አትሌቶችን መምረጥ ከባድ መሆኑን አስታውቋል።

ዓለም ካየቻቸው ምርጥ የማራቶን ሯጭ አንዱ ከሆነው ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ኦሎምፒክ እና በርካታ የአውሮፓ ሻሜፒዮን ሽፕ አሸናፊ ከሆነው ሳሙኤል ኢቶ ማንን ትመርጣላችሁ? ሲልም ኢኤስፒኤን ይጠይቃል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቻናሉ ዘገባ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ስሙ በመካተቱ እንደተደሰተ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ጽፏል።

አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ሩጫዎች የበላይነት በመያዝ እስከ 2020 ድረስ የሁለቱም ርቀቶች ሪከርዶች በእሱ እጅ ነበሩ።

ቀነኒሳ በቀለ 3 ወርቅ በኦሎምፒክ ፣ 5 ወርቅ በአለም ሻምፒዮን ሽፕ፣ 11 ወርቅ በሀገር አቋሯጭ ውድድሮች ላይ መሰብሰባ የቻለ አትሌት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ቀነኒሳ በቀለ ሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶንን ማሸነፍ ችሏል።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባም በዚህ ቻናል ምርጥ ከተባሉት አትሌቶች አንዷ ሆናለች።

አትሌት ጥሩነሽም ሶስት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨሞሮ በበርካታ አለምአቀፍ ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በዘገባው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ፣ ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኢቶ፣ የዚምባብዌዋ ዋናተኛ ክርስቲ ኮቨንትሪን እና በርካታ የፕሪሚየር ሊግ እና የአውሮፓ ሻምፒዮን ሽፕ ጨዋታዎችን ያሸነፈውን ዲድየር ድሮግባን ጨምሮ 25 ስፖርተኞች በኢኤስፒኤን ምርጥ ስፖርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአንድ ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ላይ እንደሚካፈል ተረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ የማራቶን ቡድን ውስጥ የተካተተው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና እና የ5 ጊዜ ዓለም ሻምፒዮናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ኢትዮጵያን በፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ በማራቶን ከሚወክሉ አትሌቶች መካከል አንዱ መሆን ችላል።

ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪም አትሌት ሲሳይ ለማ እና አትሌት ደረሰ ገለታ በወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው፡፡

በሴቶች ደግሞ አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ አትሌት አማኔ በሪሶ እና አትሌት መገርቱ አለሙ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሮጡ ሲሆን በሁለቱም ጾታ ሜዳሊያዎችን እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *