መንግስት በአማራ ክልል የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ተጠየቀ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ እንደ አዲስ እየተባባሱ የመጡት የሲቪክ ምህዳሩን የሚያጣብቡ ድርጊቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል።

የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን “መልሼ አደራጃለሁ” የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው።

ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል።

ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል።

ይኼውም የጸጥታ እና ደህንነት አካላት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምርመራ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እያዋከቡ ከመሆኑንም ባሻገር በቲያትር እና ጥበብ መልኩ የሚቀርቡ ሥራዎችን በማገድ እንዲሁም የቲያትር ባለምያዎቹን ለእስር የመዳረግ እርምጃዎች በተደጋጋሚ እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ካርድ ገልጿል።

በዚህም “ካርድ እነዚህ አደገኛ እና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን የሚጋፋ ድርጊቶች ተቀባይነት የላቸውም” ብሎ እንደሚያምንም አመላክቷል።

ስለሆነም መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳ፣ ሐቀኛ የተጠያቂነት ስርዓት እንዲዘረጋ እንዲሁም የሲቪክ ምህዳሩን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ ጥሪውን አቅርቧል።

እንዲሁም ካርድ “የሲቪክ ምኅዳሩን የሚያጣብቡ እርምጃዎች ዒላማ ከሆኑ ወገኖች ጋር በአጋርነት የሚቆም መሆኑን ገልጿል።

በአማራ ክልል የተከሰተውን የትጥቅ ውጊያ ተከትሎ ሐምሌ 28 ቀን 2015 የታወጀው እና በዚህ ዓመት ከጥር 28 ጀምሮ ለአራት ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከስምንት ቀናት በኋላ የጊዜ ገደቡ ይጠናቀቃል።

ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እየተካሄደ ባለበት የአማራ ክልል ውስጥ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ እንዳሉት በጦርነቱ ምክንያት ከ1 ሺህ 200 በላይ በኾኑ ኢንዱስትሪዎች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ ከስድስት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ከሥራ ገበታ ውጭ ሆነዋል ብለዋል፡፡

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊና የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በዚህ ጦርነት ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከ15 ቢሊዮን በላይ ብር የሚያወጣ ንብረት ወድሟል ብለዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ በክልሉ በተከሰተዉ ጦርነት 298 ትምህርት ቤቶች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች በጦርነቱ ምክንያት ከትምህርት ውጪ ሲሆኑ 3725 ትምህርት ቤቶች ደግሞ እንደተዘጉ ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል መናገሻ ባህር ዳር ንጹሃንን ከህግ አግባብ ውጪ ገድሏል ሲል ከሷል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *