የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ ጀመረ

አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳድጓል። ወደ ካዛብላንካ የሚደረገው የጭነት በረራ ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን ነው ተብሏል።

የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው “ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል በመልዕክታቸው።

ይህ በረራ መጀመሩ በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ የዓለም ንግድ እና ሸቀጦች ፍሰትን ለማሳለጥ አዳዲስ የጭነት መስመሮችን በመክፈት አገልግሎቱን በዓለም ዙሪያ ማስፋፋቱን እንደሚጥል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ63 በላይ ከተሞች በመብረር ላይ ሲሆን ይህም ከየትኛውም የዓለማችን አየር መንገዶች በላይ በአፍሪካ ሰማይ ላይ የሚበር አየር መንገድ አድርጎታል፡፡

በታህሳስ 1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ግብጽ ካይሮ አድርጓል፡፡

የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዱባዩ ኤርሾው ላይ ተገኝተው እንዳሉት አየር መንገዱ ከቦይንግ እና ኤርባስ 78 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማምተዋል፡፡

በ2022 ለ13 ሚሊዮን ዜጎች የበረራ መስተንግዶ የሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች እንዳሉት የገለጹት ስራ አስፈጻሚው የ2035 እቅዱን ለማሳካትም ተጨማሪ 130 አውሮፕላኖችን መግዛት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵ አየር መንገድ ከአንድ ወር በፊት 78 አውሮፕላኖችን ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ለመግዛት መስማቱ ይታወሳል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *