ኖህ ሪል ኢስቴት 754 መኖሪያ ቤቶችን አስመረቀ

ኖህ ሪል እስቴት አስረኛ ዓመቱን 754 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን በማስረከብ አክብሯል

ኖህ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር 10ኛ አመት የምስረታ በአሉን  754 አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በማስረከብ አክብሯል።

በኢትዮጵያ የከተማ ልማት ከፍተኛ እድገት አበርክቶ ያለው ኖህ ሪል ኢስቴት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ደንበኞቹና የሚዲያ አባላት ጋር አክብሯል።

ኖህ ሪል እስቴት ባለፉት አስርት አመታት 8,000 በላይ ለሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በታማኝነት፣ በሰዐቱ እና በቃሉ መሰረት አስረክቧል።

ይህ ጉዞ ኩባንያውን በኢትዮጵያ የቤቶች ልማት ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።  ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬትም ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል።

የኖህ ሪል ኢስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ንፁህ አዉግቸዉ “በዛሬው ዕለት በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን  የመኖሪያ መንደር በይፋ  ሲያስመርቅ ባለፉት አስርት አመታት የስኬት ጉዞአችን የምናከብርበት፣ እንዲሁም ወደፊት በአብሮነት ለተሻከ ስራ ቃልኪዳናችንን የምናድስበት ነው” ብለዋል።

“ኖህ ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በጊዜው እና በጥራት ገንብቶ በማጠናቀቅ በደንበኞቹ ዘንድ አመኔታን ያትረፈ ተቋም ነው” ሲሉም አክለዋል።

ኩባንያው በ2020 ዓም፣ 30,000 ቤቶችን ግንብቶ  ለማስረከብ ትልቅ ራዕይ የሰነቀ ሲሆን ፣ የመኖሪያ ቦታዎችን ወደ ሚሊዮኖች ካሬ ሜትር ለማስፋፋት አቅዶ የወደፊቱን ጊዜ በጉጉት ይጠባበቃል።

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለማልማት ከታቀደው 3,000,000 ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ሲሆን 1,000,000 ካሬ ሜትር ያህል ደግሞ የንግድ ማእከላት ለመገንባት ይውላል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀክቶች የኖህ ሪል ስቴት ለላቀ ትጋት ቀጣይነት ማሳያ ናቸው።

የኖህ ታላቅ ስኬት ዋነኛ ማሳያው 31 ፕሮጀክቶች በጥራት እና በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉ ነው። አሁን ላይ በርካታ በመካሄድ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉት ኩባንያው ከፕሮጀክቶች መካከል በጉርድ ሾላ፣ በሰሚት፣ በቦሌ ፣ በፍላሚንጎ፣ በቀበና እና በእንቁላል ፋብሪካ ያሉ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ይገኛሉ።

የኖህ ሪል ስቴት የምረቃ ዝግጅት ኩባንያው በግንባታ ዘርፍ ለአገሪቱ እድገትና ልማት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በመዘከር ጭምር የተከበረ ሲሆን በቀጣይ አስርት ዓመታትም የሚኖርቱን የስኬት ጎዞ ያስጀመረበት ነበር።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *