የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ውድድር መርሀ ግብር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት የጨዋታ እጣ ድልድልበአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሰረት ሀምበርቾ ዱራሜ ከድሬዳዋ ከተማ የመክፈቻ ውድድር ጨዋታውን የሚያደርጉ ሲሆን ሻሸመኔ ከተማ ከወላይታ ዲቻ፣ ሀዋሳ ከተማ ከፋሲል ከተማ የፊታችን መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ. ም ያደርጋሉ።

እንዲሁም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮጵያ መድህን ከከባህርዳር፣ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከመቻ የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎችን ይጫወታሉም ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ለተወዳዳሪ ክለቦች መልካም የውድድር ዓመት እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

በ2015 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ስያሜ መብትን ቤትኪንግ ይዞ እንደነበር የገለጹት ስራ አስኪያጁ የ2016 የሊግ ስያሜ መብት አሸናፊ ኩባንያ ስም በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።

ስራ አስኪያጁ አክለውም የ2015 ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ሽልማት በመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀው የፊታችን ነሀሴ 13 ቀን 2015 ዓ. ም ሀያት የሽልማት መርሀግብሩ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የ2015 ቤቲኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ64 ነጥብ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ባህርዳር ከነማ ደግሞ በ60 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን በ49 ነጥቦች የውድድር ዓመቱን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *