በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 200 ሺህ ዜጎች መሞታቸው ተገለጸ

በፈረንጆች 2022 ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብና በበሽታ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብ እና ከረሀብ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ በሽታዎች በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

በዚህም በኢትዮጵያ በረሃብና ተያያዥ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእርዳታ የሚልኩት እህል ለግል ጥቅም ሲውል እና በገበያ ላይ ሲሸጥ አረጋግጠናል በሚል የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡም፣ በዚህ ወቅት በረሃብ እና በበሽታ ለሞቱ ሰዎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል።

እንዲሁም በዚያው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ መሆኑን ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ በድኅረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የእርስ በርስ ግጭት ከምን ጊዜውም በላይ መባባሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ታጣቂዎች እና ንጹሃን መገደላቸውም ተመላክቷል።

እንደ አጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰባ ዘጠኝ አገራት ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት ከግጭት ጋር በተገያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘጠና ስድስት በመቶ መጨመሩ ነው የተገለጸው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ሲደረግ በነበረው ውጊያ ከ83 ሺሕ በላይ ዩክሬናውያን ሕይወታቸው ማለፉን እና በርካታ የአገሪቱ ዜጎች ደግሞ ለስደት መዳረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *