ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አነሳ
የጣልያኑ ኢንተርሚላንን እና የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲን ያገናኘው የዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ትናንት ምሽት በቱርክ ኢስታምቡል በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ሮድሪጎ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ጎል ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል፡፡
ማንችስተር ሲቲ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፔ ጋረዲዮላ አሰልጣኝነት ታግዞ በታሪክ የመጀመሪያውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ማንሳት ችሏል፡፡
ማንችሰተር ሲቲ በ2022/23 የውድድር ዓመት ከቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በተጨማሪ የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤካፕ ዋንጫን በማንሳት የሶትዮሽ ዋንጫ መውሰድ ችሏል፡፡
አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከባርሴሎና፣ ባየርንሙኒክ እና ማንችስተር ሲቲ ጋር አሸንፏል፡፡
ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ማንችስተር ሲቲን ከአንድ ዓመት በፊት የተቀላቀለው ኖረዌያዊው አርሊንግ ሀላንድ በ12 ጎሎች የዘንድሮው ቻምፒዮንስ ሊግ ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሮድሪ ደግሞ የፍጻሜ ውድድሩ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
የሲቲ ግብ ጠባቂው ብራዚሊያዊ ዴደርሰን ደግሞ የዘንድሮው ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ኮኮብ ግብ ጠባቂ ሆኖ አጠናቋል፡፡