ሊድስ ዩናይትድ እና ሌቺስተር ሲቲ ሳውዛምፕተንን ተከትለው መውረዳቸው አረጋገጡ

የ2022/23 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ፍፃሜውን አግኝቷል።

የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ አሸናፊ ሲሆን አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒውካስትል ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

ሊቨርፑል እና ብራይተን በቀጣይ አመት የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ሲያልፉ አስቶን ቪላ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ተሳታፊ ሆኗል።

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በ36 ግቦች የውድድሩ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።

አርሊንግ ሀላንድ ከኮኮብ ግብ አግቢነት በተጨማሪ የእንግሊዝ ኮኮብ ተጫዋች እና ወጣት ተጫዋች ሽልማትንም አሸንፏል።

ሳውዝሀምፕተን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ሌስተር ሲቲ ወደ እንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዳቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ሆነዋል።

በቀጣይ የውድድር አመት ሉተን ታውን ፣ ሼፍልድ ዩናይትድ እና በርንሌይ ወራጅ ክለቦችን በመተካት በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ክለቦች ሆነዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *